ሴፕቴምበር 26፣ 2014

SWYPE WITH DRAGON DICTATION የመጨረሻ ተጠቃሚ የፈቃድ ስምምነት

ይሕ በእርስዎ (SWYPE እና/ወይም DRAGON DICTATION መተግበሪያዎች ተጠቃሚ በሆኑት ግለሰብ ወይም ተቋም) እና NUANCE COMMUNICATIONS, INC. መካከል የተፈጸመ ሕጋዊ ስምምነት ነው። ("NUANCE")። እባክዎ የሚከተሉትን ድንጋጌዎች በጥንቃቄ ያንብቡ።

የ SWYPE ሶፍትዌርን እና/ወይም የDRAGON DICTATION አገልግሎትን ለመጫን እና ለመጠቀም በዚህ የመጨረሻ ተጠቃሚ ስምምነት ("ስምምነት") ድንጋጌዎች መስማማት አለብዎ። "ተቀብያለሁ" የሚለውን ቁልፍ በመጫን፣ በዚህ ስምምነት ድንጋጌዎች ለመገዛት ተስማምተዋል። እነዚህን ድንጋጌዎች እና የውል ሁኔታዎች እስካልተቀበሉ ድረስ በምንም አይነት መልኩ የSWYPE ሶፍትዌርንም ሆነ የDRAGON DICTATION አገልግሎትን መጠቀም አይችሉም።

የSWYPE ሶፍት ዌር እና DRAGON DICTATION አገልግሎት የጽሁፍ እና የኢሜል መልዕክት መመስረት የሚያስችሉትን ጨምሮ ተጠቃሚዎች የመሳሪያዎቻቸውን የተወሰኑ የአሰራር ሁኔታዎችን በጽሁፍ ግብዓት እና በንግግር ትዕዛዝ መቆጣጠር የሚያስችሏቸው ነገር ግን በዚህ ብቻ የማይገደቡ የተወሰኑ የደንበኛ/አገልጋይ መተግበሪያዎች አሉት። የሚከተሉት አጠቃላይ ድንጋጌዎች እና የውል ሁኔታዎች ማናቸውንም NUANCE እና አቅራቢዎቹ የሚያቀርቧቸውን እና የጽሁፍ ግብዓት የአሰራር ሁኔታን የሚሰጡ እና ተጠቃሚዎች በNUANCE መሳሪያዎች የተጫኑ የDRAGON DICTATION አገልጋይ መተግበሪያዎችን ("አገልግሎት") እንዲያገኙ እና ተጨማሪ የSWYPE ሶፍትዌሮችን ጨምሮ የSWYPE ሶፍትዌርን ("ሶፍት ዌር") እንዲሁም ሶፍትዌሩን ለመጠቀም እና አገልግሎቱን ለማግኘት የሚረዱ እና በNUANCE የተዘጋጁ አባሪ ሰነዶችን እንዲያወርዱ፣ እንዲጭኑ እና እንዲጠቀሙ ያስችሉዎታል።

1. የፈቃድ አሰጣጥ NUANCE እና አቅራቢዎቹ፣ ለእርስዎ (ለ"ባለፈቃዱ")፣በመሳሪያው ላይ በሚገኘው ሶፍትዌር አማካኝነት ሶፍትዌሩ እና አገልግሎቱ በNUANCE እና በአቅራቢዎቹ በቀረበበት አገር እና ቋንቋ ብቻ ሶፍትዌሩን በአንድ መሳሪያ ላይ ብቻ ለመጫን እና ለመጠቀም የግል፣ የብቻ ያልሆነ፣ የማይተላለፍ፣ በንዑስ ፈቃድነት የማይተላለፍ፣ ሊሻር የሚችል ውስን አና በኦብጀክት ኮድ መልክ ብቻ የሚሰጥ ፈቃድ ሰጥተዎታል። "መሳሪያ" የሚባለው በhttp://www.nuancemobilelife.com ላይ በሚገኘው የNUANCE ድር ጣቢያ ላይ በተገለጸው መሰረት የተፈቀደ ተንቀሳቃሽ ስልክ ቀፎ ነው፤ ይሕም ከጊዜ ወደ ጊዜ በNUANCE ሊሻሻል ይችላል። በተጨማሪም NUANCE ቋንቋዎችን፣ የቁልፍ ሰሌዳዎችን፣ ወይም መዝገበ ቃላትን ጨምሮ ነገር ግን በእነዚህ ብቻ ሳይወሰን ተጨማሪ የሶፍትዌር ማውረዶችን ዝግጁ እንደሚያደርግ እና እርስዎም እነዚህን ተጨማሪ የሶፍትዌር ማውረዶች በዚህ ውስጥ በቀረበው ሶፍትዌር አማካኝነት ብቻ እንደሚጠቀሙ እና የእነዚህ ተጨማሪ የሶፍትዌር ማውረድ ተግባራት አጠቃቀም በዚህ ስምምነት ድንጋጌዎች እና የውል ሁኔታዎች እንደሚገዛ አውቀው ተስማምተዋል። ከሶፍት ዌሩ እና አገልግሎቶቹ ማውረድ እና አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ለሶስተኛ ወገን (ለምሳሌ፦ Google፣ Amazon፣ Apple)፣ ለምትከፍሉት እና ከዚህ ወደ ጊዜ ሊለዋወጥ የሚችል ማንኛውም ወጪ ክፍያ ኃላፊነት የእርስዎ ነው። NUANCE በዚህ ስምምነት ውስጥ ለተቀመጠ ሶፍትዌር ወይም አገልግሎት ለሦስተኛ ወገን የሚከፈልን ማንኛውም ክፍያ ለመተካት ኃላፊነት የለበትም። በተጨማሪም ሶፍትዌሩ እና አገልግሎቱ መረጃ ለመላክም ሆነ ለመቀበል የእርስዎን ገመድ አልባ አውታረ መረብ እንደሚጠቀም እና የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት ሰጪዎም ሆነ ሌሎች ሶስተኛ ወገኖች ለሶፍትዌሩ እና አገልግሎቶቱ የአየር ጊዜ፣ መረጃ እና/ወይም ፍጆታ ክፍያ ሊያስከፍሉዎ እንደሚችሉ አውቀው ተስማምተዋል።

2. የባለፈቃዱ ግዴታዎች

2.1. ገደቦች (በሕግ ካልተፈቀደ በስተቀር) የሚከተሉትን መፈጸም አይችሉም፡ (ሀ) በNUANCE በጽሁፍ ካልተፈቀደ በስተቀር በሶፍትዌሩም ሆነ ለአገልግሎቶቹ ማናቸውንም ኦቶሜትድ ወይም የተቀዱ ጥያቄዎችን ማስረከብ፤ (ለ) ሶፍትዌሮቹን እና አገልግሎቶቹን ከራስዎ ጥቅም ውጪ ለሌላ መጠቀም፤ (ሐ) አገልግሎቱን ከሶፍትዌሩ ውጪ በሌላ ሶፍትዌር ወይም መንገድ ማግኘት፤ (መ) ሶፍትዌሩን በሙሉም ሆነ በከፊል መገልበጥ፣ ማባዛት፣ ማሰራጨት ወይም በሌላ በማናቸውም መልኩ ማባዛት ፤ (ሠ) በሶፍትዌሩ ወይም በአገልግሎቶቹ ላይ ያላችሁን ማንኛውንም መብት መሸጥ፣ ማከራየት፣ ፈቃድ መስጠት፣ በንዑስ ፈቃድ መልክ መስጠት፣ መስጠት፣ ማስተላለፍ ወይም በሌላ በማንኛውም መልክ መስጠት፤ (ረ) ሶፍትዌሩን ወይም አገልግሎቶቹን ማሻሻል፣ ማዘዋወር፣ መተርጎም ወይም ሌሎች ከውስጡ የሚመነጩ ሥራዎችን መፍጠር፤ (ሰ) የሶፍትዌሩን ወይም የአገልግሎቱን ማንኛውንም ምንጭ ኮድ፣ መነሻ ሐሳቦች፣ ወይም ስልቶች በምንም አይነት መልሶ መፍጠር፣ መበተን፣ ሪቨርስ ኢንጂነር ወይም በሌላ ሙከራ ማግኘት፣ በድጋሚ መገንባት፣ ለመለየት ወይም ለመፈለግ መሞከር፤ (ሸ) ማናቸውንም የባለቤትነት መብት መግለጫዎችን፣ ምልክቶችን ወይም አርማዎችን ከሶፍትዌሩ ላይ ማስወገድ፤ ወይም (ቀ) ሶፍትዌሩን ወይም አገልግሎቶቹን በሶስተኛ ወገኖች ከተሰሩ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ጋር እንደማወዳደሪያ ወይም ማጣጣሚያ መጠቀም።

3. የባለቤትነት መብቶች

3.1. ሶፍት ዌር እና አገልግሎት NUANCE እና ፈቃድ ሰጪዎቹ በሶፍትዌሩ እና በአገልግሎቶቹ ላይ ፓተንትን፣ የቅጂ መብትን፣ የንግድ ሚስጥር፣ የንግድ ምልክትን እና ሌሎች ተያያዥ አእምሯዊ ንብረቶችን ጨምሮ በእነዚህ ብቻም ሳይወሰን ሁሉንም መብቶች፣ ባለቤትነት እና ጥቅም በባለቤትነት ይይዛሉ እንዲሁም ከእነዚህ መብቶች ጋር የተያያዙ ማናቸውም የባለቤትነት መብት ከNUANCE እና/ወይም ከፈቃድ ሰጪዎቹ ጋር ብቻ ይቆያል። ያልተፈቀደ የሶፍትዌር ወይም የአገልግሎት ቅጂ፣ ወይም ከላይ በተጣሉት ገደቦች ያለመገዛት በቀጥታ የዚህን ስምምነት ፈራሽነት እና በስምምነቱ አማካኝነት የተሰጡ መብቶችን ቀሪነት ያስከትላል፤ እንዲሁም ለእነዚህ ጥሰቶች NUANCE ሁሉንም ሕጋዊ እና ፍትሐዊ ካሳዎችን እንዲጠይቅ መብት ይሰጣል።

3.2. የሦስተኛ ወገን ሶፍትዌር. ሶፍትዌሩ ማስታወቂያዎችን እና/ወይም ተጨማሪ ግዴታዎችን እና የውል ሁኔታዎችን የሚጠይቁ የሶስተኛ ወገን ሶፍትዌሮችን ሊይዝ ይችላል። እነዚህ ተፈላጊ የሶስተኛ ወገን ሶፍትዌር ማስታወቂያዎች እና/ወይም ተጨማሪ ግዴታዎች እና የውል ሁኔታዎች http://swype.com/attributions ላይ ይገኛሉ እንዲሁም የዚህ ስምምነት አካል ተደርገዋል እና በማጣቀሻነት ቀርበዋል። ይህንን ስምምነት በመቀበል፣ በተጨማሪነት የቀረቡትን ግዴታዎች እና የውል ሁኔታዎችን እየተቀበሉ ነው።

3.3. የንግግር መረጃ እና የፈቃድ አሰጣጥ መረጃ

(ሀ) የንግግር መረጃ እንደአገልግሎቱ አካል፣ NUANCE ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት የአገልግሎቱን እና የሌሎች የNUANCEን አገልግሎቶች እና ምርቶችን የድምጽ ጥራት ለማስተካከል፣ የድምጽ መለየትን እና ሌሎች የአገልግሎቱን ይዘቶች ለማሳደግ እና ለማሻሻል የንግግር መረጃን ይሰበስባል። የዚህን ስምምነት ድንጋጌዎች እና የውል ሁኔታዎች በመቀበል፣ NUANCE እንደ አገልግሎቱ አካል የአገልግሎቱን እና የሌሎች የNUANCEን አገልግሎቶች እና ምርቶችን የድምጽ ጥራት ለማስተካከል፣ የድምጽ መለየትን እና ሌሎች የአገልግሎቱን ይዘቶች ለማሳደግ እና ለማሻሻል የንግግር መረጃን እንዲሰበስብ እና ይሕ መረጃ ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ ለNUANCE ወይም በNUANCE ትዕዛዝ ስር ለሚሰሩ ሶስተኛ ወገኖች ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል አውቀው፣ ፈቃድ ሰጥተዋል እንዲሁም ተስማምተዋል። NUANCE በማንኛውም የንግግር መረጃ ውስጥ ያሉትን የመረጃ አካላት ከላይ ከተገለጹት ውጪ ለማንኛውም አገልግሎት አይጠቀምም። “የንግግር መረጃ” ማለት በዚህ መሰረት ወይም ከአገልግሎቱ ጋር በተያያዘ ለርስዎ የቀረቡ ወይም የድምጽ ፋይሎች፣ ተያያዥ ቅጂዎች እና ሎግ ፋይሎች ናቸው። እርስዎ የሚያቀርቡት ማንኛውም እና ሁሉም የንግግር መረጃ በሚስጥር ይያዛል፣ ነገር ግን የሕግ ወይም የደንብ መስፈርቶችን ለማሟላት ብቻ ለምሳሌ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም በሕግ የተፈቀደ ሲሆን ለመንግስት ተቋም፣ ወይም በNUANCE በሽያጭ፣ በቅልቅል ወይም በመዋሃድ ጊዜ በNUANCE ሊገለጽ ይችላል።

(ለ) የፈቃድ አሰጣጥ መረጃ እንደ ሶፍትዌሩ እና አገልግሎቱ አካል፣ NUANCE እና አቅራቢዎቹ የፈቃድ አሰጣጥ መረጃን ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ይሰበስባሉ እንዲሁም ይጠቀማሉ። እንደ ሶፍትዌሩ እና አገልግሎቱ አሰጣጥ አካል፣ NUANCE የፈቃድ አሰጣጥ መረጃን እንዲሰበስብ እውቅና፣ ፈቃድ እና ስምምነት ሰጥተዋል። የፈቃድ አሰጣጥ መረጃ NUANCE ወይም በNUANCE ትዕዛዝ ስር የሚሰሩ ሶስተኛ ወገኖች፣ በሚስጥራዊነት ስምምነት አማካኝነት ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን እንዲያለማ፣ እንዲገነባ እና እንዲያሻሽል ይረዳዋል። የፈቃድ አሰጣጥ መረጃ ከማንኛውም የተለየ ግለሰብ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስለማይፈቅድ የፈቃድ አሰጣጥ መረጃ የግል ያልሆነ፣ መረጃ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። "የፈቃድ አሰጣጥ መረጃ" ማለት ስለሶፍትዌሩ እና ስለመሳሪያዎ ያለ መረጃ ማለት ነው፡ ለምሳሌ የመሳሪያዎ የንግድ ስም፣ የሞዴል ቁጥር፣ ማሳያ፣ የመሳሪያዎ መታወቂያ ቁጥር፣ አይ ፒ አድራሻ፣ እና ተመሳሳይ መረጃዎች ማለት ናቸው።

(ሐ) ሶፍትዌሩን እና አገልግሎቶቹን በመጠቀም በውስጡ ያሉትን የንግግር መረጃ እና የፈቃድ አሰጣጥ መረጃ መሰብሰብ ተግባራት እና የሁለቱንም መረጃዎች ለNUANCE እና ለሶስተኛ ወገን የስራ አጋሮች በዩናይትድ ስቴትስ እና/ወይም በሌሎች ሐገራት ለማስቀመጥ፣ በስራ ለይ ለማዋል ወይም ለመጠቀም ፈቃድ እየሰጡ መሆኑን ተረድተዋል።

(መ) የንግግር መረጃ እና የፈቃድ አሰጣጥ መረጃ ተግባራዊ ለሚሆን የNUANCE የግላዊነት ፖሊሲ ተገዥ ናቸው። ለበለጠ መረጃ http://www.nuance.com/company/company-overview/company-policies/privacy-policies/index.htm ላይ የNUANCEን የግላዊነት ፖሊሲ ይመልከቱ።

4. ድጋፍ የሶፍትዌሩን እና የአገልግሎቶችን መገምገም እና መሞከር ሂደት ለማመቻቸት ባለፈቃዱ በNUANCE አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ከhttp://www.nuancemobilelife.comላይ መመልከት ይችላል። ለተጨማሪ ድጋፍ፣ ባለፈቃዱ ይሕንን ድጋፍ ከዚህ በፊት በተጠቀሰው ድረ ገጽ በኩል፣ እና የNUANCE ሰራተኞች በተገኙበት ሊጠይቅ ይችላል፣ NUANCE ብልሽት እና/ወይም የሶፍትዌር እና አገልግሎቶችን አሰራር እና ገጽታ ማብራሪያ በተመለከተ በፋክስ፣ በኢሜይል ወይም በሌሎች መንገዶች ለባለፈቃዱ ምክንያታዊ የሆነ የድጋፍ አገልግሎት ይሰጣል። የNUANCE ድጋፍ (የሳምንቱን የእረፍት ቀናት እና ሕጋዊ/የኩባንያውን የበዓል ቀናት ሳይጨምር) በ48 የስራ ሰዓታት ውስጥ ጥያቄዎን ይመልሳል።

5. ዋስትና ስላለመኖሩ NUANCE እና አቅራቢዎቹ ሶፍትዌሩን እና አገልግሎቶቹን ለእርስዎ የሚያቀርበው ሶፍትዌሩንና አገልግሎቶቹን እንዲጠቀሙ ለማስቻል ብቻ መሆኑን አውቀው ተስማምተዋል። በዚህም ምክንያት፣ መረጃዎን እና የአሰራር ዘዴዎን ከማንኛውም አይነት ጥፋት ወይም ብልሽት ለመጠበቅ አስፈላጊዎቹን የቅድመ ጥንቃቄ እና ደህንነት እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ተስማምተዋል። NUANCE፣ ፈቃድ ሰጪዎቹ እና አቅራቢዎቹ ሶፍትዌሩን እና አገልግሎቶቹን ከነስህተታቸው፣ እና ያለምንም አይነት ዋስትና"ባሉበት ሁኔታ"ያቀርባሉ። አግባብ በሆነ ሕግ እስከሚፈቀድበት ከፍተኛ ወሰን ድረስ፣ NUANCE፣ ፈቃድ ሰጪዎቹ እና አቅራቢዎቹ የመሸጥ አቅምን፣ ለአንድ አገልግሎት ተስማሚነትን፣ ወይም የጥሰት አለመኖርን ጨምሮ ማንኛውም አይነት በግልጽም ሆነ በውስጥ ታዋቂነት የተሰጠ ዋስትና አለመኖሩን በተለየ ገልጸዋል።

6. የሃላፊነት ውስንነት አግባብ በሆነ ሕግ እስከሚፈቀድበት ከፍተኛ ወሰን ድረስ፣ NUANCE፣ የስራ ኃላፊዎቹ፣ ዳይሬክተሮቹ፣ እና ሰራተኞቹ፣ አቅራቢዎቹ ወይም ፈቃድ ሰጪዎቹ ለማንኛውም ቀጥታ፣ ተዘዋዋሪ፣ ልዩ፣ በአጋጣሚ የሚከሰረት፣ ተያያዥ ወይም ተከታይ ጉዳቶች እንዲሁም በዚህ ብቻ ሳይወሰን ነገር ግን የሚከተሉትን ጨምሮ፣ ከሶፍትዌሩ ወይም አገልግሎቶቹ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ለቀረ ገቢ፣ ለጠፋ መረጃ፣ ለጥቅም ማጣት፣ ለንግድ መቋረጥ፣ የሽፋን ወጪ የሚከፈል ካሳ፣ ጉዳቱ እንደሚደርስ ምክር ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ወይም አስቀድሞ ማወቅ ነበረበት የሚባል ቢሆንም እንኳን በማንኛውም አጋጣሚ ለተከሰተ ጉዳት ኃላፊነት የለባቸውም።

7. ውሉ የሚቆይበት እና የሚቋረጥበት ጊዜ ይሕ ስምምነት የዚህን ስምምነት ግዴታዎች እና የውል ሁኔታዎች በተቀበሉትን ጊዜ ወዲያው ይጀምርና ሲቋረጥ ደግሞ የቆይታ ጊዜው ያበቃል። NUANCE በማንኛውም ጊዜ በራሱ ስልጣን፣ በምክንያትም ሆነ ያለምክንያት የአገልግሎቶቹ ጊዜ ማብቃቱን ወይም መቋረጣቸውን ለርስዎ በማሳወቅ ይሕንን ስምምነት እና/ወይም በዚህ ስምምነት አማካኝነት የተሰጡ ሌሎች ፈቃዶችን ሊሰርዝ ይችላል። ይሕ ስምምነት እርስዎ ማናቸውንም ግዴታዎቹን ወይም የውል ሁኔታዎችን በጣሱ ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል። ይሕ ስምምነት ሲቋረጥ፣ በአፋጣኝ መጠቀምዎትን መቆም እና ሁሉንም የሶፍትዌሩን ቅጂዎች ማጥፋት አለብዎ።

8. ወደ ውጪ የመላክ ደንብ ማክበር። እርስዎ ለሚከተሉት ዋስትና ይሰጣሉ (ቀ) በዩኤ.ስ መንግስት ማዕቀብ የተጣለበት ወይም በዩኤስ መንግስት "አሸባሪዎችን የሚደግፍ"ተብሎ የተፈረጀ አገር ውስጥ የሚኖሩ አለመሆንዎን፣ እና (ii) በማናቸውም የዩኤስ መንግስት የተከለከሉ ወይም የተገደቡ ወገኖች ዝርዝር ውስጥ አለመካተትዎን።

9. የንግድ ምልክቶች በሶፍትዌሩ ወይም በአገልግሎቶቹ ውስጥ የሚገኙ ወይም ጥቅም ላይ የዋሉ የሶስተኛ ወገን የንግድ ምልክቶች፣ የንግድ ስሞች፣ የምርት ስሞች እና ምልክቶች ("የንግድ ምልክቶቹ") እያንዳንዳቸው የየባለቤቶቻቸው ንብረቶች ሲሆኑ እነዚህን የንግድ ምልክቶች መጠቀም ለንግድ ምልክቱ ባለቤት የሚጠቅም መሆን አለበት። እነዚህን የንግድ ምልክቶች መጠቀም የጋራ አሰራርን ለመወከል የታቀደ ሲሆን የሚከተሉትን አያካትትም (ቀ) NUANCE ከተጠቀሰው ኩባንያ ጋር ዝምድና ያለው መሆኑን (ii) NUANCE እና ምርቶቹ ወይም አገልግሎቶቹ ይህንን ኩባንያ መቀበላቸውን ወይም ማጽደቃቸውን።

10. ገዢ ሕግ ይሕ ስምምነት በሕጎች ግጭት መርሆቹ ሳይመራ በኮመንዌልዝ ኦፍ ማሳቹሴትስ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ሕግ ይገዛል፣ እናም እርስዎም በዚህ ስምምነት አማካኝነት ለሚነሱ ማናቸውም አለመግባባቶች ለተባለው የኮመንዌልዝ የፌደራል እና ግዛት ፍርድ ቤቶች የብቻ ስልጣን ተገዢ ይሆናሉ። ይሕ ስምምነት ተግባራዊነቱ በዚህ ስምምነት መሰረት በግልጽ በገለለው በተባበሩት መንግስታት የአለም አቀፍ የእቃዎች ሽያጭ ስምምነት ተገዢ አይሆንም።

11. ሊለወጡ የሚችሉ የውል ግዴታዎች NUANCE ኢሜይል አድራሻዎን ጨምሮ በተመዘገቡበት ወቅት በሰጡት አድራሻ መሰረት ለርስዎ ምክንያታዊ የሆነ ማስታወቂያ በመስጠት የዚህን ስምምነት ግዴታዎች እና የውል ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊለውጥ እንደሚልችል አውቀው ተስማምተዋል። በዚህ ስምምነት ውስጥ ለሚደረጉ ለውጦች ካልተስማሙ፣ ያለዎት ብቸኛ መፍትሔ ሶፍትዌሩን እና አገልግሎቶቹን መጠቀምዎን ማቆም ነው። NUANCE እነዚህን ለውጦች እንዲገመግሙ ምክንያታዊ የሆነ ማስታወቂያ ከላከልዎ በኋላ በሶፍትዌሩ ወይም በአገልግሎቱም ሆነ በማንኛውንም ክፍል መጠቀምዎን ከቀጠሉ ለውጦቹን እንደተቀበሉ ይቆጠራል።

12. አጠቃላይ የሕግ ድንጋጌዎች ከNUANCE በቅድሚያ የጽሁፍ ፈቃድ ካላገኙ በስተቀር በዚህ ስምምነት ያገኙትን መብት ወይም ግዴታ ለሌላ ወገን መስጠት ወይም በማናቸውም መንገድ ማስተላለፍ አይችሉም። በእርስዎ እና በNUANCE መካከል ያለው አጠቃላይ ስምምነት በዚህ ስምምነት ውስጥ ያለው ነው እናም ስለሶፍትዌሩ የተደረጉ ሌሎች ማናቸውንም ግንኙነቶች ወይም ማስታወቂያዎች ይሽራል። የዚህ ስምምነት ማንኛውም ድንጋጌ ዋጋ የሌለው ወይም ተፈጻሚ የማይሆን ሆኖ ከተገኘ፣ ይህ ድንጋጌ ዋጋ አልባነቱ እንዲቀር እና ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለብቻው ይታረምና የተቀሩት የስምምነቱ ክፍሎች በሙሉ ሐይል እና ውጤት ይቀጥላሉ። NUANCE በዚህ ስምምነት መሰረት ያገኛቸውን መብቶቹን ወይም ድንጋጌዎችን ሳያስፈጽም መቅረቱ እነዚህን መብቶች ወይም ድንጋጌዎች እንደተወ አያስቆጥርም። የዚህ ስምምነት ክፍል 2፣ 3፣ 5፣ 6፣ 7፣ 9፣ 10 እና 12 ድንጋጌዎች ይሕ ስምምነት ከተቋረጠም በኋላ ተፈጻሚ ይሆናሉ።